“ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር
ዘምሩ!”
መዝሙር 96:1
በክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን ፣ በፅዮን ድምፅ አገልግሎት በግንቦት ወር የሚዘጋጅ በአይነቱ ልዩ የሆነ ዓመታዊ ኮንፍራንስ ሲሆን ዓላማውም እግዚአብሔርን ስለ ታላቅነቱ፣ ገናናነቱ፣ ልዕልናው የምንወድስበት እንዲሁም ቅዱሳን ሁላችን እግዚአብሄር ያረገልንን ሁሉ በማስታወስ ጽፈን መተን ስለ እያንዳንዱ የአባታችን መልካምነት እና የማዳኑ ክንድ የምናመሰግንበት እግዚአብሄርንም በከበረ መንገድ የምናከብርበት ድንቅ ቀን ነው።
በዚህ ዕለት የህይወታችን አንደኛው እና ዋነኛው አካል እና መገለጥ የሆነውን የአምልኮን ህይወት እንዲሁም ለህይወታችን የብዙ በረከት ደጆች ምክኒያት የሆነውን የምስጋና ህይወት እንካፈል ዘንድ መልካሙን የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን በልዩ ልዩ የስነ-ጥበብ ስራዎች ደግሞ የፅዮንን የህይወት ስርዐት እንካፈላለን።
በአንድ ልብ እና መንፈስ ሆነን ለክብር ንጉስ ሀሌሉያ እንል ዘንድ ተቀላቀሉን!